
ወልድያ: የካቲት 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ.ር) በሰሜን ወሎ ዞን ሀራ ከተማ አሥተዳደር የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
የሀራ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ሰኢድ የከተማው የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ከሕዝብ ቁጥሩ ጋር ተመጣጣኝ ባለመኾኑ ነዋሪዎች እየተቸገሩ መኾኑን ገልጸዋል። ይህንን ለመቅረፍ ከተማ አሥተዳደሩ ሥራዎችን እያከናወነ ስለመኾኑም ጠቁመዋል።
የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ.ር) ከተማ አሥተዳደሩ ለውኃ ማስፋፊያ የሰጠው ትኩረት አበረታች ነው ብለዋል።
የሀራ ከተማን ጨምሮ እንደክልል ያለውን የንጹህ መጠጥ ውኃ እጥረት ለመቅረፍ ቢሮው በትኩረት እየሠራ ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!