
የአማራ ክልል አምራች ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ከፍተኛ መነቃቃትን አሳይቷል፡፡
በክልሉ በነበረን ቆይታ የአማራ ብረታብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝን የስራ ሂደት ተመልክተናል።
ኢንተርፕራይዙ በተሰማራባቸው የብረት ማቅለጥ፣ የማሽነሪ ምርት፣ የኮሪደር ዲች ከቨሮች፣ ስማርት ፖሎች ማምረት፣ የትራንስፎርመር እና የእርሻ መሣሪያዎችን በመገጣጠም ለክልሉ የልማት ስራዎች መፋጠን ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡
በተለይም ተኪ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባለፈ የልማት ስራዎች በግብዓት እጥረት እንዳይስተጓጎሉ እያገዘ ነው፡፡
አምራቾች ለተኪ ምርት ትኩረት በመስጠት ሀገራዊ ግባችን እንዲሳካ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው፡፡
