የሰላምና የፀጥታ ሥራዎችን በዘላቂነት ለማጽናት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ የሰሜን ወሎ ዞን አሳሰበ።

31

ባሕር ዳር: የካቲት 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን አሥተዳዳር ያለፉት ወራት የፓለቲካ፣ የሰላም፣ የፀጥታ፣ የልማትና የመልካም አሥተዳዳር ሥራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በግምገማ መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ውኃ ቢሮ ኀላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ደጀኔ ልመነህን፣ እና ሌሎችም የክልል እና የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር የሰላምና የፀጥታ ሥራዎችን በዘላቂነት ለማጽናት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል። ከአማራ ኮሚዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በራስ አቅም የማድረግ አቅምን በማጠናከር እና ዘላቂ ሰላምን በመትከል ሕዝብን ማገልገል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሕዝብ ተመራጮች በጎንደር ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
Next articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦