
ባሕር ዳር: የካቲት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር የክልል ምክር ቤት ተመራጮች የመራጭ ተመራጭ መድረክ ተካሂዷል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በመንግሥት መሪነት እና በማኅበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ የከተማዋን የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ መመለስ ይገባል ብለዋል።
የሕዝብ ወኪሎች ውክልናቸውን በአግባቡ ለመወጣት እየሠሩ ስለመኾኑም ገልጸዋል። የዜጎችን የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ጥያቄዎች በውይይት እና በሃሳብ የበላይነት መፈታት ይኖርባቸዋልም ነው ያሉት።
መንግሥት፣ የፀጥታ መዋቅሩ እና ማኅበረሰቡ ተቀናጅተው በሠሩት የተጠናከረ ተግባር ለአካባቢው ሰላም መረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል።
የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ አሚን የሱፍ የከተማዋን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በፌደራል መንግሥት እና በከተማ አሥተዳደሩ ትብብር በርካታ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!