ሚዛኑን የጠበቀ ልማት እና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በፖለቲካው የሴቶች ተሳትፎ ጎልቶ መታየት አለበት።

22

አዲስ አበባ: የካቲት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ብልጽግና ሴቶች ክንፍ 1 ሺህ 500 የአመራር አባላት በተገኙበት የብልጽግና ጉባዔ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች እና የክንፉ ሚና ላይ ውይይት እያደረገ ነው።

በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሞገስ ባልቻ በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳይ የፍትሐዊነት ጉድለትን ለማጥበብ እና ለማረም ክንፉ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።

በቁጥር 5 ሺህ 300 ከሚደርሰው የአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራር 32 በመቶ የሚኾኑት ሴቶች ናቸው ያሉት ኀላፊው ይህ ደግሞ ሚዛኑን የጠበቀ ልማት እና ተጠቃሚነት እንዲኖር ያግዛል ብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የነበረው ሴቶች ክንፍ በሚል የስያሜ ለውጥ ማምጣቱን የተናገሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ዛህራ ሁመድ ከዚህ በፊት በሊጉ ውስጥ የተወሰኑ ክልሎች ብቻ በዋና አመራርነት ይሳተፉ እንደነበር አንስተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
Next articleየኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር ከስዊድን ፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በፍልሰት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።