
እንጅባራ: የካቲት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንጅባራ ከተማ የተገነቡ የመሠረተ ልማቶች እና ወደ ሥራ የገቡ የተለያዩ ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች በፌዴራል፣ በክልሉ፣ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ እንዲኹም በከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ መሪዎች ዛሬ ተጎበኝተዋል።
ከተጎበኙ የመሠረተ ልማት ሥራዎች መካከል የዱቄት ፋብሪካዎች፣ የሳሙና ማምረቻ ፋብሪካ፣ የሆቴል ኢንቨስትመንት ግንባታዎች፣ የትራፊክ ኮምፕሌክስ ግንባታዎች ይገኙበታል።
ከጉብኝቱ ባሸገር በከተማዋ ባለሀብቶች የሚገነቡ የየታሸገ ውሃ ማምረቻ ፋብሪካ እና ባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ሆቴል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ እና ሥራውን የማስጀመር መርሃ ግብር ተካሂዷል።
ዘጋቢ፦ ሰሎሞን ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!