“ዕቅዳችን እና መዳረሻችን ኢትዮጵያን ያማከለ ሰው ተኮር ተግባር መኾን አለበት” መሉነሽ ደሴ (ዶ.ሴ)

22

ባሕር ዳር: የካቲት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሴቶች ክንፍ አባላት በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባዔ በተወሰኑ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።

“የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አባላት እንዲሁም የደጋፊዎች ሚና” በሚል መሪ መልእክት ነው ውይይቱ እየተካሄደ ያለው።

የውይይቱ የክብር እንግዳ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ሥራ አስፈጻሚ እና የሲዳማ ክልል አፈ ጉባዔ ፈንታየ ከበደ እንዳሉት ፓርቲው በፈተና ውስጥ ኾኖም በልማት፣ በመልካም አሥተዳደር እና በፖለቲካ ዘርፍ ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርጉ ሥራዎች አከናውኗል።

ኢትዮጵያን እየገነቡ ያሉ ብዙ ጀግና ሴቶች አሉ ያሉት አፈ ጉባዔዋ ፈተናዎችንም ወደ ዕድል እና ድል የሚቀይሩት ብዙ ናቸው ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኀበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) አማራጭ ሀገር ስሌለን ያለችንን አንድ ሀገር በጋራ መገንባት አለብን ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ በመልዕክታቸው “ዕቅዳችን እና መዳረሻችን ኢትዮጵያን ያማከለ ሰው ተኮር ተግባር መኾን አለበት” ነው ያሉት።

በውይይቱ ላይ ከፌዴራል እና ክልሎች የተወከሉ የሥራ ኀላፊዎች ተኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየገጠር መንገድ ትስስርን ተደራሽ ለማድረግ ወደ ሥራ ተገብቷል።
Next articleየማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና ተጠያቂነቱ