ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎበኙ።

43

ባሕር ዳር: የካቲት 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጉብኝቱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ለወጣቶች የሥራ እድል የፈጠሩ፣ የሃብት ተጠቃሚነትንም ያሳደጉ መኾናቸውን ገልጸዋል።

በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የልማት ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ መቀጠላቸውን ተመልከተናል ነው ያሉት።

በከተማዋ ከትንናት ጀምሮ ያደረጓቸው ጉብኝቶች ከተማዋ ወደ መደበኛ ሰላሟ መመለሷን እና የልማት ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ እየቀጠሉ መኾናቸውን ተመልክተናል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦
Next articleየገጠር መንገድ ትስስርን ተደራሽ ለማድረግ ወደ ሥራ ተገብቷል።