የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት፦

63

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ግንባታ በአስደናቂ የማጠናቀቂያ የግንባታ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

ስታዲየሙ ባለፈው ሐምሌ ላይ ስንመጣ ከነበረው ገፅታ በእጅጉ ተለውጦ ምድረ ግቢው የተሻለ አምርቶ የተመልካች ወንበሮች ገጠማ እየተፋጠነ፣ ሳሩ ተተክሎ እና ሌሎች የውስጥ ሥራዎች እየተሠሩ ተመልክተናል።

የስታዲዬሙ ግንባታ በሁሉም መሠረተ ልማቶች የካፍ እና ፊፋን ዓለም አቀፍ ደረጃ ጠብቆ በመጨረሻው የግንባታ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

ግዙፉ የባሕር ዳር ስታዲዬም ሀገራችን አሕጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን እንድታስተናግድ ዕድል የሚፈጥር ነው። በተጨማሪም ለባሕር ዳር ከተማ ተጨማሪ ውበት፣ የገቢ ምንጭ እና የስፖርት ዘርፉ መነቃቃት እንዲኖረው የሚኖረው አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው።

በዚህ ዓመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር በውይይታችን አይተናል።

Previous articleባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዓድዋ ድልን 129ኛ ዓመት በተለያዩ ኹነቶች እያከበረ ነው።
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕር ዳር የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎበኙ።