የዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች ሕዳሴ ግድብን ጎበኙ።

24

ባሕር ዳር: የካቲት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም አቀፍ እና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች እና ከፍተኛ የግድብ ደኅንነት ባለሙያዎች የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

በውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ድኤታ አብርሃ አዱኛ (ዶ.ር) በተመራው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉብኝት የተፋሰሱ ሀገራት ኮሚሽነሮች እና ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የካናዳ የግድብ ማኅበር፣ የአውስትራሊያ የትልልቅ ግድቦች ማኅበር፣ የኖርዌይ የሀይድሮፓወር ማኅበር እና ከዛምቢያ የዛምቤዚ ወንዝ ባለስልጣን አመራሮች ተሳትፈዋል።

ጉብኝቱ በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘውና በናይል ተፋሰስ የግድብ ደኅንነት ማዕከል ለማቋቋም የሚመክረው ዓለም አቀፍ የምክከር መድረክ አካል መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የካቲት 15 የናይል ቀን በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት የተፋሰሱ ሀገራት ሚኒስትሮችና ጋዜጠኞች ሕዳሴ ግድብን መጎብኘታቸው ይታወቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሃይማኖት አገልጋዮች በሕዝቦች አንድነት፣ ሰላም፣ ፍትሕና እኩልነት ላይ አጥብቀዉ ማስተማር እንደሚጠበቅባቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ።
Next articleየልማት ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ የምርምር ሥራዎችን እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አስታወቀ።