በሕገ ወጥ መንገድ የተከዘነ 200 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ።

83

ባሕር ዳር: የካቲት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ በሕገ ወጥ መንገድ በመጋዘን ላይ የነበረ የአፈር ማዳበሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ሚሊሻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

የአፈር ማዳበሪያው የተያዘው በማኅበረሰቡ ጥቆማ መኾኑም ተገልጿል።

በከተማዋ የሚፈጸሙ መሰል ወንጀሎችን ለመከላከል ማኅበረሰቡ ለፀጥታ ኅይሉ እያደረገ ያለውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቁን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምክር ቤት አባላት የሕዝብ ውክልናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተጠየቀ።
Next articleተጀምረው ሳይጠናቀቁ የቆዩ ግንባታዎችን መልክ የማስያዝ ሥራ እየተሠራ ነው።