የምክር ቤት አባላት የሕዝብ ውክልናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ተጠየቀ።

45

እንጅባራ: የካቲት 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክር ቤት የኮሶበር የምርጫ ክልል ተመራጮች ከእንጅባራ ከተማ እና ባንጃ ወረዳዎች ከተወጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም ውይይቱ ለሀገር ብልጽግና የሚበጁ ጠቃሚ ሐሳቦችን ለማመንጨት እና ችግሮቻችን እንዲፈቱ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የመብራት ሰብስቴሽን ግንባታ መዘግየት፣ የወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ፣ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ መዘግየት፣ የጸጥታ ችግር፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ የጤና ተቋማት የግብዓት አቅርቦት ማነስ፣ የእንጅባራ ከተማ የደረጃ ሽግግር፣ ግንባታቸው የተጀመሩ የአስፋልት መንገዶች ግንባታቸው መጓተት እና ሌሎችም ችግሮች ሊፈቱላቸው እንደሚገባ ተሳታፊዎቹ ጠይቀዋል።

የምክር ቤት አባላት የኅብረተሰቡን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ የሕዝብ ውክልናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም ተሳታፊዎቹ አንስተዋል። የአማራ ክልል ምክር ቤት የኮሶበር ምርጫ ክልል ተመራጭ አየን ብርሃን ውይይቱ የክልል ምክር ቤት ተመራጮች በዓመት አንድ ጊዜ ከመረጣቸው ሕዝብ ጋር በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚያደርጉት የውይይት አካል መኾኑን ተናግረዋል።

ከኅብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎች በተዋረድ ባለው የመንግሥት መዋቅር ቀርበው እንዲፈቱ እንደሚደረጉም አቶ አየን ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleማኅበረሰቡን በሥርዓት እና በሕግ መምራት ያስፈልጋል።
Next articleበሕገ ወጥ መንገድ የተከዘነ 200 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ።