ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ባሕርዳር ገቡ።

54

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ባሕርዳር ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሕርዳር ሲገቡ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎችን ባሕርዳር ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሕርዳር በሚኖራቸው ቆይታ የባሕርዳርን የኮሪደር ልማት፣ የባሕርዳርን ስታዲየም እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ ተብሏል።

Previous article“በናይሮቢ ከተማ በኦብነግ ስም የወጣው መግለጫ ድርጅቱን ፈፅሞ አይወክልም” የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር
Next articleማኅበረሰቡን በሥርዓት እና በሕግ መምራት ያስፈልጋል።