ዓድዋ የአንድነት፣ የመፈቃቀር፣ የመተጋገዝ እና የጀግንነት በዓል መኾኑን የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

34

ደሴ: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ መልዕክት በኮምቦልቻ ከተማ በጎዳና ላይ ትርዒት እና በልዩ ልዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ተከብሯል። አሚኮ ያነጋገራቸው የበዓሉ ታዳሚዎች የዓድዋ ድል የአንድነት፣ የመፈቃቀር፣ የመተጋገዝ እና የጀግንነት በዓል መኾኑን ገልጸዋል። ድሉ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው ብለዋል።

አያቶቻችን ዘር፣ ብሔር እና ሃይማኖት ሳይለያቸው ወራሪውን ኀይል መክተው ድል የነሱበት፤ ኢትዮጵያዊ በሙሉ የዘመተበት እና ድል ያደረገበት በዓል መኾኑን ተናግረዋል። የዓድዋ ድል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሰባስቦ በጋራ ያመጣው ድል ነው ብለዋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሳይነጣጠል በአንድነት ሊያከብረው ይገባል ነው ያሉት።

የኮምቦልቻ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሁሴን አሕመድ የዓድዋ ድል ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደ አቅሙ የተሳተፈበት ድል መኾኑን ገልጸዋል። ዛሬ ላይ ዓድዋን ስናከብርም ኾነ ወደ ፊትም የተለያዩ ሥራዎችን ሥንሰራ ልክ እንደ አያቶቻችን አንድነታችንን ጠብቀን እና ተባብረን መኾን አለበት ነው ያሉት።

ዘጋቢ:- መስዑድ ጀማል

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአንድ ስንኾን ከራሳችን አልፈን ለአፍሪካ ኩራት እንደምንኾን ዓድዋ ማሳያ ነው።
Next articleየዓድዋ ድል በዓል በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው።