
ደሴ: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በደሴ ከተማ በድምቀት ተክበሯል። የበዓሉ ተሳታፊዎች በዓሉ የመላ ኢትዮጵያዊያን ድል መኾኑን ተናግረዋል። በዓሉን ስንዘክር አሰባሳቢ ትርክትን በመገንባት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ዓድዋ በዘመን ሂደት የማይደበዝዝ ኢትዮጵያዊያን ከአራቱም አቅጣጫ ተሰባስበው ያስመዘገቡት የጥቁር አፍሪካውያን የነፃነት አርማ የታተመበት አንፀባራቂ ድል ነው ብለዋል።

አንድነት ያስከብራል ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ለድል አድራጊነትም መሠረታዊ መሣሪያ መኾኑን ነው የተናገሩት። “ኢትዮጵያውያን አንድ ስንኾን ከኢትዮጵያ አልፈን ለአፍሪካ ኩራት መኾን እንደምንችል ዓድዋ ማሳያ ነው” ብለዋል።
ከዓድዋ ድል በመማር የውስጥ ችግሮቻችንን በውይይት በመፍታት፣ አንድነታችን በማጠናከር ዕድገታችን ማሳለጥ እና ሉዓላዊ ክብራችን ማስጠበቅ ይኖርብናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
ዘጋቢ ፦አንተነህ ፀጋዬ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
