
ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች 129ኛውን የዓድዋ ድል በዓል አስመልክተው ለኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ የዓድዋ ድል አንድነት እና ብሔራዊ ኩራትን የሚገልጽ ነው ብሏል።
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለኢትዮጵያ ብልጽግና እና ስኬትን ተመኝቷል።
በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሁለቱ ሀገራት በታሪክ ጀግንነትን፣ አንድነትን እና ጽናትን የሚጋሩ መኾናቸውን ጠቅሷል። ሀገራቱ ከታሪኮቻቸው ባሻገር መጪዎቹ ጊዜያት ብሩህ እንደሚኾኑም እምነቱን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያዊያን የጽናት እና የአንድነት ምልክት መኾኑን በመግለጽ ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት እንዲኾን መልካም ምኞቱን ገልጿል። በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የእንግሊዝ፣ የጀርመን እና የኩባን ጨምሮ የተለያዩ ኤምባሲዎች ለበዓሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል በሀገር ውስጥ እና በተለያዩ የዓለም ሀገራት በሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!