“የዓድዋ ድል የ19ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ጦርነት እና ድል ነው” ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው

32

ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 129ኛ የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ነው።

የዓድዋ ድል ምስጢር ኢትዮጵያውያን ስለሀገራቸው ክብር ያሳዩት ፍጹም አንድነት መኾኑን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ገልጸዋል፡፡

ድሉ የአፍሪካውያን የአርነት ትግል እና የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ እንዲፋፋም ትልቅ ጉልበት መኾኑንም አስታውቃል፡፡

“የዓድዋ ድል የ19ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ጦርነት እና ድል ነው” ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የዓድዋ ድል የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበረ እና የአሸናፊነት ሥነ-ልቦናን ያጎናጸፈ ድል እንደኾነም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የኢትዮጵያውያን ተጋድሎ እና የአሸናፊነት ምስጢር”
Next articleየተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።