
ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ተከብሯል።
በዓሉ በሕንድ ኒው ዴልሂ የኢትዮጵያ ሚሲዮን፣ በእስራኤል ቴል-አቪቭ፣ በጂቡቲ፣ በአልጄሪያ አልጀርስ፣ በቤልጂየም ብራሰልስ፣ በኬንያ ናይሮቢ፣ በደቡብ ሱዳን ጁባ እና በሌሎች ሀገራትም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በተለያዩ መርሐ ግብሮች ነው የተከበረው።
የመከላከያ ሠራዊት አታሼዎች፣ በየሀገራቱ ያሉ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች እና የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!