“የዓድዋ ድል በአንድነትና ትብብር የአፍሪካን መፃኢ ዕድል የተሻለ ማድረግ እንደሚቻል ማሳያ ነው” ሙሳ ፋቂ ማህማት

20

ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዓድዋ ድል የጥቁር ኅዝቦችን የይቻላል አስተሳሰብ ያሰረፀ መኾኑን የቀድሞው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት ገለጹ። 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ኅዝቦች ድል” በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተለያዩ መርኃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።

የቀድሞው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት በበዓሉ አከባበር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የዓድዋ ድል ጦርነትን የማሸነፍ ታሪክ ብቻ አይደለም ብለዋል። የዓድዋ ድል ጦርነትን የማሸነፍ ታሪክ ብቻ አለመሆኑን ጠቅሰው፤ ለመላ ጥቁር ኅዝቦች የይቻላል አስተሳሰብን ያሰረፀ ነው ብለዋል።

የዓድዋ ድል በአንድነትና ትብብር የአፍሪካን መፃኢ ዕድል የተሻለ ማድረግ እንደሚቻል ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል። አፍሪካ ለደረሰባት በደል ካሳ የምትጠይቅበት ዓመት እንደመሆኑ በዓሉ ትልቅ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑንም አንስተዋል።

አፍሪካውያን ከተባበሩና በአንድነት ከቆሙ ይሳካ የማይመስሉ ድሎችን ማስመዝገብና የተሻለ አህጉር ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚችሉም አንስተዋል። ኢትዮጵያ የነፃነት ቀንዲልና የአፍሪካውያን ተምሳሌት መሆኗንም በቅርቡ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች እየታዩ ያሉ የልማት ሥራዎች ምስክር ናቸው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዓድዋ የምንዘክረው ታሪክ ብቻ ሳይኾን ለትውልድ የምናወርሰው ታላቅ ኀላፊነት ነው” ኢንጅነር አይሻ መሐመድ
Next article“የማይጠልቅ ጀምበር፣ የማያረጅ መንበር”