
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ መልእክት የተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
በብራስልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ በኬንያ እንዲሁም በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲና በሌሎችም በዓሉ እየተከበረ ይገኛል፡፡
በኤምባሲዎቹ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች እና በሀገራቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በዓሉን በሚዘክሩ የተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ መሆኑም ታውቋል፡፡