“የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያውያንን ልክ የሚያሳይ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት ነው ዓድዋ” አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ

17

ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ ለዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አፈጉባኤው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዓድዋ የኢትዮጵያዊያን የጀግንነት፣ የአልበገር ባይነት፣ የአርበኝነት፣ የአትንኩኝ ባይነት፣ እምቢ ለባርነት ተጋድሎ ልዩ ምልክት ነው ብለዋል። የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያውያንን ልክ የሚያሳይ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት ነው ዓድዋ ነው ያሉት።

መላው ኢትዮጵያውያን በዘር በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ በአንድነት የተዋደቁበት የሀገራችንን ክብር በደምና በአጥንት የሕይወት መስዋዕትነት ለትውልድ ያቆዩበት እጅግ ልዩ ታሪክ ነው ብለዋል።

የዛሬው ትውልድ ከትናንትናው የአባቶቹ ገድል በመማር ሀገርንና ሕዝብን ከሚያዋርድ ድህነት ለመላቀቅና ሀገራችንን ለማበልጸግ አርዓያነት ያለው ተግባር መፈፀም አለብን ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዓድዋ ድል የሀገር እና የትውልድ ክብር ተጠብቋል” አቶ ይርጋ ሲሳይ
Next article“ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ” የመከላከያ ሚኒስቴር