“በዓድዋ ድል የሀገር እና የትውልድ ክብር ተጠብቋል” አቶ ይርጋ ሲሳይ

16

ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ ለዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አቶ ይርጋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን ብለዋል።

በዓድዋ ድል የሀገር እና የትውልድ ክብር ተጠብቋል። የቀኝ ገዥዎች ምኞት መክኗል ነው ያሉት። በቀኝ ግዛት ቀንበር ውስጥ ለነበሩ ጥቁር የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ተስፋና ኩራት መሆን ችሏል። በዘመናት ሁሉ የትውልዱ የድል አክሊል ኾኖ ይኖራል ብለዋል ። የዓድዋ ድል ከአያሌ የጀግንነትና የመስዋዕትነት ታሪኮቻችን መካከል የተለየ ቦታ የምንሰጠው ልዩ የድል በዓላችን ነው። እኛ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ከተባበርን ምንም አይነት ኀይል ሊበግረን እንደማይችል ዘላለማዊ ምስክር ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

ከምንም በላይ ደግሞ የአንድነትና የነፃነት አርማ የሆነውን የዓድዋ ድል እየዘከርን አሰባሳቢውን የብሔራዊነት ገዥ ትርክት ለመገንባትና ኅብረ ብሔራዊ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንደምሰሶ ሁኖ ያገለግለናል። የትናንቱን ጀግንነት ለዛሬው የብሔራዊነት የአርበኝነት ስንቅ አድርገን ልንጠቀምበት ይገባል ነው ያሉት።

ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለዓድዋ ድል ጀግኖቻችን ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article” አባቶቻችን በዘመናት ርዝማኔ የማይደበዝዝ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article“የኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያውያንን ልክ የሚያሳይ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት ነው ዓድዋ” አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ