
ባሕር ዳር: የካቲት 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ለዓድዋ የድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።
በዓድዋ ጦርነት ሀገራችንን ለማስከበር እና ነፃነታችንን ለማስጠበቅ ሲሉ አባቶቻችን ታላቁን መስዋዕትነት ከፍለዋል። በዘመናት ርዝማኔ የማይደበዝዝ ታላቅ ድልም አስመዝግበዋል ነው ያሉት። ይኸም ተመን የማይገኝለት ለትውልዶች ሁሉ ያበረከቱት እጅግ ውዱ ስጦታ ነው ብለዋል።
ይህ ትውልድም ለሀገረ መንግሥት ግንባታና የኢትዮጵያዊነት ልዕልና ማፅኛ የኾነውን የብሔራዊነት ትርክትን በመገንባት የድርሻቸውን ሊወጣ ይገባል ነው ያሉት። ርእሰ መሥተዳድሩ ለበዓሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!