“ጠንካራ የቀበሌ መዋቅር ካለ ጠንካራ ሀገር መፍጠር ይቻላል”

47

ባሕር ዳር፡ የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን በስማዳ ወረዳ እና በወገዳ ከተማ አሥተዳደር “ቀበሌዎቻችን በማፅናት ሁለንተናዊ እምርታ እናስመዘግባለን” በሚል መሪ መልዕክት ለቀበሌ መሪዎች የሚሰጠው ሥልጠና ተጀምሯል።

በሥልጠናው የተገኙት የደቡብ ጎንደር ዞን ውኃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ በለጠ ተስፌ የክልላችን እና የሀገራችን ሰላምና ልማት እንዲም የሕዝባችን የመልማት ፍላጎት የሚረጋገጠው ጠንካራና ቁርጠኛ የመሪ መዋቅር መፍጠር ሲቻል ነው ብለዋል።

ለሕዝቡ የእርካታ ምንጭ በመኾን በኩል ሰፊውን ድርሻ የሚይዘው የቀበሌ መሪ መዋቅር ነው ያሉት አቶ በለጠ ደካማ የቀበሌ መወቅር ካለ ደካማ ሀገር ይፈጠራል፤ ጠንካራ የቀበሌ መዋቅር ካለ ጠንካራ ሀገር መፍጠር ይቻላል ብለዋል።

ሥልጠናው ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቆይ ነው። ብቁ እና ጠንካራ የቀበሌ መሪ በመፍጠር ከሰላም እጦት መውጣት አስፈላጊ መኾኑ ተገልጿል።

“ቀበሌዎቻችን በማፅናት ሁለንተናዊ እምርታ እናስመዘግባለን” በሚል መሪ መልዕክት የተዘጋጀ የቪዲዮ ሥልጠና በክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እየቀረበ መኾኑን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያሳያል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article”ሴት የሥራ መሪዎች የተገኘውን እድል በመጠቀም ጠንክሮ መሥራት ይገባናል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)
Next article”ለሴቶች ተጠቃሚነት ትላንትን ሳይኾን ነገን እያሰብን መሥራት ይገባል” ወይዘሮ ብርቱካን ሲሳይ