“በቀበሌዎች ላይ የሚካሄዱ የውይይት ሀሳቦች እና ስትራቴጂዎች ቀበሌዎችን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ” የሀራ ከተማ አሥተዳደር

25

ወልድያ: የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ሀራ ከተማ አሥተዳደር “ቀበሌዎቻችንን በማጽናት ሁለንተናዊ እመርታ እናስመዘግባለን” በሚል መሪ መልዕክት ለቀበሌ መሪዎች ሥልጠና መሥጠት ተጀምሯል።

የሀራ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ሰኢድ እንደተናገሩት ቀበሌዎች የዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት ማዕከል እና የልማት መሠረት ናቸው ብለዋል።

የቀበሌዎች ጥንካሬ የከተማው ጥንካሬ መሠረት ሲኾን የቀበሌው ዕድገት የከተማው አጠቃላይ ዕድገት መሠረት ነው ብለዋል።

በሥልጠናው የሚዳብሩት የውይይት ሀሳቦች እና ስትራቴጂዎች ቀበሌዎችን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ትልቅ ሚና ይጫወታሉም ነው የተባለው።

የሀራ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ፈንታው በለጠ ሥልጠናው ከንድፈ ሀሳብ ባለፈ በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ ተመስርቶ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል አቅም የሚገነባበት፣ ልምድ የሚለዋወጥበት እና የጋራ ራዕይን ለማሳካት የሚያስችል ዕቅድ የሚወጣበት እንደኾነም አስረድተዋል።

ሥልጠናው ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መኾኑን ከከተማ አሥተዳደሩ ለማወቅ ተችሏል።

ዘጋቢ፦ ካሳሁን ኃይለሚካኤል

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ቀበሌዎቻችን የከተማችን ሁለንተናዊ መሰረቶች ናቸው” የወልድያ ከተማ አሥተዳደር
Next articleበአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ባቲ ወረዳ የቀበሌ መሪዎችን ለማብቃት ያለመ ሥልጠና እየተሰጠ ነው።