
ወልድያ: የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ቀበሌዎቻችንን በማፅናት ሁለንተናዊ እምርታ እናስመዘግባለን” በሚል መሪ መልዕክት የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ለቀበሌ መሪዎች ሥልጠና እየተሰጠ ነው።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ቀበሌዎቻችን የከተማችን ሁለንተናዊ መሰረቶች ናቸው ብለዋል። በመኾኑም ሰላምን ለማፅናት ቀበሌዎች ላይ እግርን መትከል ወሳኝ መኾኑን አስረድተዋል።
የሥልጠና ተሳታፊዎች የቀበሌያቸውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ሰላምን በሕዝባቸው እንዲያሰርፁ አደራ ብለዋል።
በሥልጠናው ላይም በነፃነት ሀሳብ እንዲያጋሩ እና ለተግባራዊነቱ ቁርጠኛ ኾነው እንዲሳተፉ አሳስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን