በክህሎት እና በአስተሳሰብ የተቀራረበ የቀበሌ መሪ አፈጻጸም እንዲኖር እየተሠራ ነው።

13

ደሴ: የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ቀበሌዎቻችንን በማጽናት ሁለንተናዊ እምርታ እናስመዘግባለን” በሚል መሪ መልዕክት በደሴ ከተማ ለቀበሌ መሪዎች ሥልጠና እየተሰጠ ነዉ፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የደሴ ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኅላፊ አሸናፊ አለማየሁ በከተማ አሥተዳደሩ ለሚገኙ የ26 የከተማ እና የገጠር ቀበሌ መሪዎች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና መጀመሩን ገልጸዋል። ሥልጠናዉ ለሦሥት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይም ተናግረዋል፡፡

ዜጎች በርካታ ማኅበራዊ እና አሥተዳደራዊ አገልግሎት የሚያገኙት ቀበሌ ላይ ነው ያሉት አቶ አሸናፊ አገልግሎቱን ለማሣለጥ የቀበሌ መሪዎች በክህሎት እና በአስተሳሰብ የተቀራረበ አፈጻጸም እንዲኖራቸዉ ሥልጠናዉ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተደደር አማካሪ ባዘዘው ጫኔ በበኩላቸዉ ብልጽግና ፓርቲ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በሁለተኛዉ የፓርቲ ጉባኤ ላይ አቅጣጫዎችን ካስቀመጠ በኋላ በወሳኝ ወቅት እየተሰጠ ያለ ሥልጠና ነዉ ብለዋል፡፡

የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ እንዲኹም የፓርቲዉን እና የመንግሥትን አቅጣጫዎች እና ዉሳኔዎች ለማስፈጸም መሪው ወሳኝ ኀላፊነት አለበት ያሉት አቶ ባዘዘዉ የቀበሌ መሪው ደግሞ በተለየ ኹኔታ ከሕዝብ ጋር የሚገናኝ በመኾኑ ሥልጠናው አስፈላጊ ስለመኾኑ ተናግረዋል፡፡

ለቀበሌ መሪዎች እየተሰጠ ያለዉ ሥልጠና በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ አቶ ባዘዘው ጠቁመዋል፡፡

ዘጋቢ:- ከድር አሊ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ትውልድን ለማሻገር ከቀበሌ ጀምሮ የመሪዎችን አቅም ማጎልበት አስፈላጊ ነው” የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር
Next article“የዓድዋ ድል በዓል የነጻነታችን አርማ ከፍ ብሎ የተሰቀለበት ልዩ ቀን ነው” የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር