
ባሕር ዳር: የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በሚገኙ ሁሉም የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር ማዕከላት “ቀበሌዎቻችንን በማፅናት ሁለንተናዊ እመርታ እናስመዘግባለን” በሚል መሪ መልዕክት የጠቅላላ ቀበሌ መሪዎች ሥልጠና በድምቀት ተጀምሯል።
የቀበሌ መሪዎች የሥልጠና መድረክ ዓላማ የመሪዎችን አቅም መገንባት፣ የአካባቢያቸውን ፀጋ ተጠቅሞ ሰላም እና ልማትን የሚያረጋገጥ እና የመሪነት ሚናውን በአግባቡ የሚወጣ የቀበሌ መሪ ለመፍጠር ያለመ ነው።
ሥልጠናው መላ የቀበሌ መሪዎችን አቅም በመገንባት በቀበሌዎች የተጀመረውን የእግር መትከል ተግባራት አጠናክሮ ለመሄድ ግብ አስቀምጧል።
የሥልጠና መድረኩ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚሰጥ ነው። መፍጠርን እና መፍጠንን የተገነዘበ የቀበሌ መዋቅር ለመገንባት፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን በፍጥነት ምላሽ የሚሰጥ የቀበሌ መሪ ለመፍጠር ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።
የአማራ ክልልን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ የተደራጀ የሕዝብ ተሳትፎን የማረጋገጥ፣ የፖለቲካ እና የፀጥታ መዋቅሩን በማቀናጀት የሕግ ማስከበር ተግባሩን በውጤት የመለካት ብሎም የቀበሌ መሪዎችን ተልዕኮና ሚናን ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!