የዓድዋ ድል በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ በፓናል ውይይት እየተከበረ ነው።

33

ደብረ ብርሃን: የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 129ኛው የዓድዋ የድል በዓል በደብረ ብርሃን ከተማ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ ወርቃለማው ኮስትሬ የዓድዋ የድል ታሪክ የድል እና የአይበገሬ በዓላችን ነው ብለዋል።

ትውልዱ የአባቶቹን ታሪክ ለማስቀጠል የበኩሉን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ ተክለየስ በለጠ ዓድዋ የጥቁሮች ነጻነትና እኩልነት የተረጋገጠበት የድል በዓል ነው ብለዋል።

ይህንን ታላቅ መሰዋእትነት የተደረገበት የድል በዓላችንን ወጣቱ ትውልድ ጠብቆ ማቆየት ይገባዋል ነው ያሉት።

ዓድዋ ከእቴጌ ጣይቱ ብልሃትንና ጥበብ የተሞላበት መሪነትን የምንማርበት ነው ብለዋል።

በዓሉ በፓናል ውይይት እና በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች በደብረ ብርሃን ከተማ እየተከበረ ነው።

ዘጋቢ:- ፋንታነሽ መሐመድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቀበሌ መሪዎች ከሕዝብ ጋር በመቀናጀት ሰላምን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ተገለጸ።
Next articleየጥበበኞች ተጋድሎ በዓድዋ!