“እንኳን ለረመዳን ጾም አደረሳችሁ” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

21

ባሕር ዳር: የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የረመዳንን ጾም አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንኳን ለረመዳን ጾም አደረሳችሁ፤ ወደ ፈጣሪ የምንቀርብበት፣ ወገኖቻችንን የምንረዳበት፣ ለሀገራችን ሰላምና ለሕዝባችን አንድነት የምንጸልይበት ወቅት እንደሚኾን ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

ረመዳን ጾም እና ዐቢይ ጾም በተመሳሳይ ወቅት ውለዋል። ይሄም ለሀገራችን በረከት እንደሚሆን አምናለሁ ነው ያሉት። ተባብረንና ተግባብተን መኖር እንዳለብን እያስተማሩንም ይሆናል! ማን ያውቃል? ብለዋል።
መልካም የረመዳን የጾም ጊዜ ይሁን ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየማዕከላዊ ጎንደር ዞን እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ ሰነዶችን ለመረካከብ ተስማሙ።
Next articleበወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሰላም፣ ልማት፣ ሕግ እና ሥርዓት እንዲረጋገጥ እየተሠራ ነው።