በጫካ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።

88

ባሕር ዳር: የካቲት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በላይ ጋይንት ወረዳ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 13 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል። የጨጨኾን ቀበሌ ጨምሮ በወረዳው ባሉ የተለያዩ ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጣቂ ቡድን አባላት አሁን ሁሉም ስለገባን ሕዝቡን ለመካስ ተመልሰናል ብለዋል።

በመደናገር ሕዝብን ሲበድሉ መቆየታቸውን ገልጸዋል። ከሕዝባችን ጋር ኾነን እንታገላለን፤ ሕዝባችንም እንክሳለን ነው ያሉት። እየተበደለ ያለው ሕዝባችን ነው ያሉት ታጣቂዎቹ ተደናግረው ጫካ በመግባት ሕዝብን እየበደሉ ያሉ ሁሉ መንግሥት የሰጠውን የሰላም አማራጭ ተጠቅመው በሰላም እንዲገቡ እና የሕዝቡን ስቃይ እና ሰቆቃ እንዲቀንሱም ጥሪ አቅርበዋል።

የላይ ጋይንት ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መርሻ አበጀ ሕዝባችን ተጎሳቁሏል፤ የሚያስፈልገው ልማት ነው ብለዋል። ከግጭት ትርፍ የለም ያሉት ኀላፊው ሌሎች የታጠቁ ኃይሎችም ዕድሉን በመጠቀም መግባት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። የላይ ጋይንት ወረዳ አሥተዳዳሪ ግርማ ይስማው በሕዝቡ መከራ እና እንግልት በመጸጸት ሰላማዊ አማራጭን መጠቀማቸው ጥሩ እርምጃ መኾኑን ገልጸዋል።

ሳይገባቸው ታጥቀው ሕዝብን እና ሀገርን እየበደሉ ያሉ ዕድሉን እንዲጠቀሙ እና እንዲገቡም ጥሪ አቅርበዋል። የደቡብ ጎንደር ዞን ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ እና የላይ ጋይንት ወረዳ እና የነፋስ መውጫ ከተማ አሥተዳደር ደጋፊ ወንዴ መሠረት የሕዝባችን ጥቅም ማስከበር የሚቻለው አንድነትን በማጠናከር ነው ብለዋል። ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን የተገነኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር ሰላማዊ መንገድን መጠቀም ይገባል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በኑሯቸው ላይ ለውጥ እንዲመጣ ማድረጉን አርሶ አደሮች ተናገሩ።
Next article“አንድነታችንን በማጠናከር እና የወል ትርክትን በመገንባት የዘመኑ አርበኛ ልንኾን ይገባል” አየለ አናውጤ (ዶ.ር)