“የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ መደበኛው ሁኔታ ተመልሷል” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

18

አዲስ አበባ: የካቲት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሞቃዲሾ ያደረጉት ጉብኝት ሀገራቱ ከነበሩበት ውጥረት ወጥተው ወደ መደበኛው ሁኔታ እየተመለሱ ስለመኾኑ ማሳያ ነው ብለዋል።

ሁለቱ ሀገራትም አልሸባብን ለመዋጋት፣ በጋራ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር፣ ኢትዮጵጵያ በአሚሶም ሰላም ማስከበር የምትሳተፍበት ሁኔታ ላይ መስማማት መቻሉን ጠቅሰዋል። ይህ የሁለቱ ሀገራት ስምምነት ከራሳቸው አልፎ ለቀጣናው ሰላም ጠቃሚ ነው ብለዋል። ቃል ዓቀባዩ በብራዚሊያ ስለተደረገው የብሪክስ ዋና እና ምክትል አስተባባሪዎች ጉባኤ እና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ሥራ መሠራቱንም ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- አንዱዓለም መናን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደሴ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የአሚኮ ሚዲያ ኮምፕሌክስ በጥራት እና በፍጥነት እየተከናወነ ነው።
Next article“ዓድዋ የጽናት፣ የአንድነት እና የሀገር ኩራት ነው” የአሜሪካ ኤምባሲ