
ደሴ: የካቲት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአሚኮ እና የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የሥራ ኀላፊዎች በግንባታው ሂደት ላይ የክትትል ጉብኝት ያካሄዱ ነው። በጉብኝቱ የግንባታው ፕሮጀክት ሥራ አሥኪያጅ ዳንኤል ኃይለማርያም እና የአሚኮ ደሴ ፕሮጀክት አማካሪ ተስፋዬ አበጋዝ ግንባታው በጥራት እና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥኪያጅ ታደሰ ግርማ ኮርፖሬሽኑ በክልሉ እና ከክልሉ ውጭ የተለያዩ ግንባታዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የአሚኮን የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታም በጥራት እና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
የአሚኮ የኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ሥራ አሥፈጻሚ አስቻለው አየሁዓለም ግንባታውን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በክትትል ጉብኝቱ ላይ የተገኙት የሥራ ኀላፊዎች ግንባታው በመሪዎች ክትትል መደረጉ በጥራት እና በፍጥነት እንዲገነባ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፦ ሕይዎት አስማማው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!