ዓድዋ አባቶች በመስዋዕትነት ያቆዩት ታሪክ የማይሽረው ስጦታ ነው።

32

ደሴ: የካቲት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዓድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይኾን ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ተምሳሌት ነው። ዘንድሮ 129ኛው የዓድዋ ድል በዓል “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ መልዕክት እየተከበረ ይገኛል። የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአሚኮ በሰጡት አስተያየት፣ ዓድዋን ሲያስቡ ኩራት እና ደስታ እንደሚሰማቸው ገልጸዋል። አያት ቅድመ አያቶቻቸው ይህን ታላቅ ድል ሊያስመዘግቡ የቻሉት በአንድነት በመቆም እና ለአንድ ዓላማ በመታገል ነው።

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ ተስፋ ዘውዱ “እኛ አላፊዎች በመኾናችን የማያልፍ ሀገር እና የሚቀጥል ትውልድ በመኖሩ ዓድዋን ከእነሙሉ ክብሩ አውቀነው ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ አለብን” ብሏል። በወሎ ዩኒቨርሲቲ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ተመራቂ ተማሪ ሄኖክ ኃይሌ በበኩሉ፣ ዓድዋን የእኛ ትውልድ በአግባቡ ተረድቶት እና ተምሮበታል ብሎ እንደማያምን እና በዓመት አንድ ጊዜ ቀኑን ጠብቆ ማክበር ብቻ ሳይኾን ታሪኩን በአግባቡ ተረድቶ የነገዋ ኢትዮጵያን የሚገነባ ትምህርት መቅሰም ይገባል በማለት አሳስቧል።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የዓድዋን ታሪክ አስፈላጊነት በመገንዘብ፣ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ቁርጠኝነታቸውንም አሳይተዋል።

ዘጋቢ፡-መሃመድ በቀለ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጀመረው መሠረታዊ የተቋም ለውጥ ፈጣን፣ ዘላቂ እና ውጤታማ እንዲኾን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረበ።
Next articleትላንት አባቶች በደም እና በአጥንታቸው ያጸኗትን ሀገር ወጣቱ ትውልድ ሊጠብቃት ይገባል።