የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጀመረው መሠረታዊ የተቋም ለውጥ ፈጣን፣ ዘላቂ እና ውጤታማ እንዲኾን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረበ።

50

ባሕር ዳር: የካቲት 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ላከናወናቸው ሥራዎች ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመሥግኗል።

በሥነ ሥርዓቱ መልዕክት ያስተላለፉት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ዓለምአንተ አግደው የአማራ ክልል ምክር ቤት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጀመረውን መሠረታዊ የተቋም ለውጥ ሥራ ፈጣን ዘላቂ እና ውጤታማ ለማድረግ በሕግ ማዕቀፍ የተደገፈ እንዲኾን ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል። የወጡት ሕጎች በወጡበት አግባብ ተተግብረው ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ የባለድርሻ አካላት እውቅና እና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ማስፈለጉን ተናግረዋል።

በየደረጃው የሚገኙ ባላ ድርሻ አካላት የጸደቁ ሕጎችን ለመተግበር እንዲተባበሩም ጠይቀዋል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዳኝነት ሥርዓቱን ለማዘመን ላከናወናቸው ሥራዎች አበርክቶ የነበራቸው አካላትን አመስግነዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች እና ሌሎች የሕግ ባለሙያዎች ላደረጉት ድጋፍም እውቅና ሰጥተው አመስግነዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የአትክልትና ፍራፍሬ ችግኞች ማዘጋጀቱን የምዕራብ ጎጃም ዞን ገለጸ።
Next articleዓድዋ አባቶች በመስዋዕትነት ያቆዩት ታሪክ የማይሽረው ስጦታ ነው።