
ባሕር ዳር: የካቲት 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባዘጋጀው የምስጋና እና የትውውቅ ሥነ ሥርዓት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ ተገኝተዋል። የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓቱን ለማሻሻል ባለፉት ጊዜያት ወጥተው በጸደቁ አዋጆች ላይ የትውውቅ እና የድርጊት መርሐ ግብርም ይከናወናል።
በሥነ ሥርዓቱ የክልሉ ምክር ቤት እና የክልሉ መሥተዳድር ምክር ቤትን ጨምሮ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የዳኝነት እና የፍትሕ ሥርዓቱን የማሻሻል ሥራዎች ሂደት ለነበራቸው አበርክቶ እውቅና እና ምስጋና ይሰጣቸዋል ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!