ዑለማዎች ለሀገረ ሰላም እና ለሕዝቦች አንድነት በትኩረት እንዲሠሩ ተጠየቀ።

73

አዲስ አበባ: የካቲት 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለሁለት ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማዎች 3ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቋል። በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ዑለማዎች ለሀገረ ሰላም እና ለሕዝቦች አንድነት እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ዑለማዎች ለሀገረ ሠላም፣ ዕድገት፣ አንድነት፣ ፍቅር እና ክብር እንዲጎለብት ወሳኝ መኾናቸውን ገልጸው ለዚህም በትኩረት እንዲሠሩ አሳስበዋል። የሮመዳንን ወር በተለይም በተፈጥሮ አደጋ የተፈናቀሉ ወገኖችን በዱአ በማሰብ ማሳለፍ እንደሚገባም ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የዑለማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት፣ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ባለ 14 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

ዘጋቢ:- ቴዎድሮስ ደሴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በተደጋጋሚ በተሠሩ ሥራዎች የክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መጥቷል” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
Next articleቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን አስታወቀ።