ኢትዮ ቴሌኮም ለኢንተርፕራይዝ ደንበኞች አስፈላጊ የኾኑ ሰባት አዳዲስ አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ።

62

አዲስ አበባ፡ የካቲት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ የዲጂታል ሶሉሽኖችን ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ ይገኛል። አገልግሎቶቹ ለኅብረተሰቡ ሁለንተናዊ ለውጥ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ትልቅ ትርጉም የሚያመጡ እና የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን ብሎም የፋይናንሺያል አካታችነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።

አሁን ላይም ተቋሙ አሠራሮችን ለማዘመን እና ቢዝነሶች ለደንበኞቻቸው የላቀ አገልግሎት በማቅረብ ቀጣይነት ያለው እድገት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ ሰባት አገልግሎቶችን ተግባራዊ ማድረጉን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።

አገልግሎቶች የእንስሳት ምርታማነትን እና የመከታተያ ዘዴዎችን የሚያሳድግ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት ኮር ባንኪንግ፣ የፋይናንሺያል፣ የትምህርት አመራር ሥርዓት፣ የአንድ ቢሮ ትብብር እና ምርታማነት፣ ቴሌ ኮንታክት ሴንተር፡ የደንበኞችን ተሳትፎ እና የድጋፍ አገልግሎቶችን ማሻሻል ኢ.አር.ፒ ሶሉሽኖች በተቀናጀ የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ቢዝነሶችን ማጎልበት ላይ ትኩረት አድርገው የሚሠሩ ናቸው ብለዋል።

እነዚህ ተግባራዊ የኾኑ አገልግሎቶችን የሚጠቀሙ ደንበኞች ሥራን ፈጣን እና ጥራት ያለው እንዲኾን ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ እና ችግሮችን የሚፈቱ መኾናቸውን ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ ራሔል ደምሰው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ትልቁ ሃብት ሰብዓዊ ሃብት ነው” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next articleከ3 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ተማሪዎች የምገባ መርሐ ግብር ተጀምሯል።