በልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 27 ባንኮች ተሳተፉ።

59

ባሕር ዳር: የካቲት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ 27 ባንኮች መሳተፋቸውን አስታውቋል። ባንኮቹ በአማካይ 1 የአሜሪካን ዶላር ለመግዛት 135 ነጥብ 6185 ብር ማቅረባቸውን ገልጿል።

ብሔራዊ ባንክ በልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታው ላይ በርካታ ባንኮች መሳተፋቸው መልካም የሚባል መኾኑን አመልክቷል። በቀጣይ ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ገበያ ሁኔታን በቅርበት በመከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ሽያጮችን እንደሚያካሂድ ማሳወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

ባንኩ በነሐሴ ወር 2016 ዓ.ም በተመሳሳይ የልዩ ውጪ ምንዛሬ ጨረታ ማካሄዱ የሚታወስ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ኢንዱስትሪዎች በትስስር ሊሠሩ ይገባል ተባለ።
Next article243 ቢሊዮን ብር ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተጥቷል።