
እንጅባራ: የካቲት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 31ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው የአሥፈጻሚ ተቋማትን የ2017 በጀት ዓመት የባለፉትን ስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እያዳመጠ ነው።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሙሉዓዳም እጅጉ ቀጣይነት ያለው እድገት ለማስመዝገብ ሰላምን እያረጋገጡ ልማትን ማፋጠን ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። “እየተሻሻለ የመጣውን ሰላም ለማጽናት የመንግሥት ቁርጠኝነት እና የኅብረተሰቡ አጋርነት ሊጠናከር እንደሚገባም” አንስተዋል።
የገቢ አሠባሠብን በተመለከተ ኅብረተሰቡ ከሚያነሳው የመልማት ጥያቄ አንጻር አናሳ በመኾኑ ትኩረት መደረግ አለበትም ብለዋል። በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በርካታ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መኾናቸውን ያነሱት አፈ ጉባዔዋ መላው የምክር ቤት አባላት ህጻናት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!