በደብረ ብርሃን ከተማ አምስት ፍብሪካዎች ሥራ ጀመሩ።

70

ደብረ ብርሃን: የካቲት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር አምስት ፍብሪካዎችን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። የተመረቁት ፋብሪካዎች የመኪና ባትሪ፣ የስፓንጅ ውጤቶች፣ የንጽህና መጠበቂያ፣ የዱቄት እና የጅብሰም ማምረቻዎች ናቸው ።
በደብረ ብርሃን ከተማ በዚህ ዓመት ብቻ ያሁኑን ጨምሮ 10 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 17 ፍብሪካዎች ወደ ምርት ገብተዋል ነው የተባለው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ እንድሪስ አብዱ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ: ለዓለም ለይኩን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የልጆቼን መልክ ዛሬ አየሁ” ታካሚ እናት
Next articleከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ገቢ ተሠብስቧል።