ኢትዮጵያ በብዝኃነት አያያዝ ልምድ የሚወሰድባት ሀገር መኾኗን የሞሮኮ ልዑካን ገለጹ።

31

ባሕር ዳር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሞሮኮው መሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ሰክሬተሪ መሐመድ ረፊቅ (ዶ.ር) የሚመራው ልዑክ ከሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ጋር የሁለቱን ሀገራት መልካም ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

ልዑካኑ ኢትዮጵያ የቀደመ ሥልጣኔ ያላት ጥንታዊት ሀገር እንደመሆኗ ብዙ ልምዶችን ማካፈል እንደምትችል በማሰብ ለልምድ ልውውጥ መምጣታቸውን ገልጸዋል። በብዝኃነት አያያዝ በተለይም ቤተ እምነቶች በሰላም እና በአብሮነት ለጋራ ሰላም እና ተጠቃሚነት የሚሠሩበት ሁኔታ ለሀገራቸው ሞሮኮ ጥሩ ልምድ እንደሚኾን ተናግረዋል፡፡

የሞሮኮ መሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን በ48 የአፍሪካ ሀገራት ቅርንጫፎችን መክፈቱን ያነሱት ልዑካኑ በኢትዮጵያም ቅርንጫፍ ለመክፈት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ኢትዮጵያ ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት እና ፍትሐዊነት የምታስተናግድበት ሕገ መንግሥት መኖሩ፤ ከአድሏዊነት ነፃ የኾነ የመንግሥት አገልግሎት የሚሰጥበት ሥርዓት መዘርጋቱ በመካከላቸው ሰላማዊ የኾነ ግንኙነት ማጠናከሩን ገልጸዋል።

ከሰላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የቀረበውን ቅርንጫፍ የመክፈት ጥያቄ ወደ ፊት ምላሽ የሚሰጥ መኾኑን ገልጸውላቸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ600ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገለጸ።
Next articleብሔራዊ ባንክ ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ነገ ያካሂዳል።