ከ600ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገለጸ።

44

ባሕር ዳር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለ2017/18 የምርት ዘመን ግብዓት የሚውል 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል። ከዚህ ውስጥ 614 ሺህ 865 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን እስከ የካቲት 16/2017 ዓ.ም ድረስ ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገልጿል።

በጅቡቲ ወደብ 12 መርከቦች ላይ 640ሺህ 795 ነጥብ 1 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ተጭኖ መድረሱ ተመላክቷል። ከዚህ ውስጥ 614ሺህ 865 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዟል ነው የተባለው።

ወደ ሀገር ውስጥ ከተጓጓዘው ማዳበሪያ ውስጥ 90ሺህ 965 ሜትሪክ ቶን በባቡር፣ 523 ሺህ 900 ነጥብ 2 ሜትሪክ ቶን በደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች መጓጓዙን ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደቡብ ጎንደር ዞን በመስኖ ልማት ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።
Next articleኢትዮጵያ በብዝኃነት አያያዝ ልምድ የሚወሰድባት ሀገር መኾኗን የሞሮኮ ልዑካን ገለጹ።