
ደብረታቦር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ እና ሊቦ ከምከም ወረዳዎች በመስኖ እየለማ ያለ ሰብል ተጎብኝቷል።
በደቡብ ጎንደር ዞን በተያዘው የምርት ዘመን ከ47 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት ታቅዶ እስካሁን የዕቅዱን 93 በመቶ ማልማት እንደተቻለ የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ ለአሚኮ ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ 29 ሺህ 400 ሄክታር መሬት በቆላ ስንዴ ለምቷል ነው ያሉት።
በተያዘው የመስኖ ሥራ በሁሉም የሰብል አይነቶች ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅም አብራርተዋል።
ዘጋቢ፦ አስፋው ሙቀት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!