ከ500 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ ገለጸ።

40

ባሕር ዳር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የሰባት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አወቀ ዘመነ የተቋሙን አደረጃጀት እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ለማጠናከር መሠራቱን ገልጸዋል። ከአጋር አካላት ጋርም በቅንጅት ለመሥራት ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰዋል።

ለ1 ሚሊዮን 233 ሺህ 744 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል። ለ510 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውንም ገልጸዋል። 70 በመቶ የሚኾኑት በቋሚ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው መኾናቸውንም አመላክተዋል። 68 ሺህ 175 ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋም አቅደው እየሠሩ መኾናቸውን አንስተዋል። 20 ሺህ 901 ኢንተርፕራይዞች መደራጀታቸውንም ገልጸዋል።

በሕገ ወጥነት የተያዙ 2 ሺህ ሸዶች እና 3 ሺህ ኮንቴይነሮች መለየታቸውን የጠቀሱት ምክትል ኀላፊው እስካሁን 841 ሸዶች እና 957 ኮንቴይነሮች መመለሳቸውን ገልጸዋል። የማስመለስ ሥራውም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ለ780 ሺህ ዜጎች በውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እስካሁን ለ40 ሺህ 123 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችላል ነው ያሉት። የሥራ ዕድል ፈላጊዎችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠራም ገልጸዋል።

ከርካታ ተቋማት ጋር በትብብር እየተሠሩ መኾናቸውንም ተናግረዋል። የተገኘው ውጤትም የየተቋማቱ ጭምር መኾኑን አንስተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል መሥተዳድር ምክርቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።
Next articleበደቡብ ጎንደር ዞን በመስኖ ልማት ከአንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።