“ትልቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የኅብረተሰብ ተሳትፎ ሚናው ጉልህ ነው” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

53

ባሕር ዳር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው። የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፈቃዱ ተሰማ ኅብረ ብሔራዊ እና ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባት የኅብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መኾኑን ገልጸዋል።

ኅብረተሰቡ በሀገሩ ጉዳይ ንቁ ተሳፎ ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል። የተመዘገቡ ድሎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አንስተዋል። ያለ ህዝብ ተሳትፎ ድልን ማሳካት እንደማይቻል የተናገሩት ኀላፊው የሀገርን ሰላም እና ልማት ለማረጋገጥ የሁሉንም ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) የሀገርን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ በትብብር መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

“ትልቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የኅብረተሰብ ተሳትፎ ሚናው ጉልህ ነው” ብለዋል። ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በፓርቲው የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ለማሳካት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኮሪደር ልማቱ ለ37 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
Next articleየሰላም ጥሪን መቀበል እና ሰላምን አማራጭ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።