የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የፌዴራል ባለድርሻ አካላት በአጀንዳ ማሰባሰብ ላይ የሚሳተፉበትን መድረክ ሊያዘጋጅ ነው።

17

ባሕር ዳር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በፌዴራል ደረጃ በምክክር ሂደቶች እንዲሳተፉ ከለያቸው ባለድርሻ አካላት ጋር አጀንዳ ለማሰባሰብ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በሂደቱም ኮሚሽኑ በፌዴራል ደረጃ ከሚገኙ ተቋማት እና ማኅበራት አጀንዳ ይሰበስባል ተብሏል። መርሐ ግብሩም በአዲስ አበባ ከተማ በቅርቡ እንደሚከወን ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ድረ ገጽ ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኮሚሽኑ ላለፉት ወራት በአስር ክልሎች እና ሁለት የከተማ አሥተዳደሮች አጀንዳ ሲያሰባስብ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ በቅርቡ በአዲስ አበባ በሚካሄደው መድረክ በድምሩ 17 ከሚኾኑ የፌዴራል ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ አጀንዳዎችን ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡ በሂደቱም የሚከተሉት ባለድርሻ አካላት ጥሪ ተደርጎላቸዋል። ተቋማቱ በወኪሎቻቸው አማካኝነት በሂደቱ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

👉የሃይማኖት ተቋማት
👉 የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን
👉 የአረጋውያን ማኅበራት ፌዴሬሽን
👉 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲ) መምህራን
👉 የመምህራን ማኅበር
👉 የአሠሪዎች ፌዴሬሽን
👉 የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን
👉 ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች
👉 ታዋቂ ሰዎች
👉 የፌዴራል መንግሥት
👉 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
👉 የፌዴሬሽን ምክር ቤት
👉 የፌዴራል ፍርድ ቤት
👉 የሀገር መከላከያ ሠራዊት
👉 የፌዴራል ፖሊስ
👉 የፌዴራል ንግድ ምክር ቤት
👉 የሴቶች እና የወጣቶች ማኅበራት ፌዴሬሽን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዓድዋ የአንድነታችን ማሰሪያ ውል ነው።
Next articleበኮሪደር ልማቱ ለ37 ሺህ ሰዎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።