በሆሳዕና ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

32

ባሕር ዳር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ውይይቱ ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው።

በውይይቱ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፈቃዱ ተሰማ ፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች መገኘታቸውን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበወልቂጤ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።
Next articleዓድዋ የአንድነታችን ማሰሪያ ውል ነው።