
ባሕር ዳር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወልቂጤ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው። ውይይት ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ያተኮረ ነው።
በውይይቱ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታሁን አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ውይይቱ ብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር የሚያስችል ነው ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!