የጦጢቶ ተንጠልጣይ የእግረኛ ድልድይ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።

51

ባሕር ዳር: የካቲት 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ)በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ 02 ቀበሌ ጦጢቶ ወንዝ ላይ የተገነባው ተንጠልጣይ ድልድይ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል፡፡ 120 ሜትር ርዝመት ያለው ተንጠልጣይ ድልድዩ በ11 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር መገንባቱ ተመላክቷል።

ደልድዩ በክልሉ መንግሥት እና ሔልቬታስ ስዊስ ኢንተርናሽናል በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት የተሠራ መኾኑንም ተገልጿል። ተንጠልጣይ ድልድዩ ለሚቀጥሉት 50 ዓመታት እንዲያገለግል ታስቦ የተሠራ መኾኑን ተመላክቷል።

ከአማራ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የድልድዩ መገንባት በክረምት ወቅት በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ይደርስ የነበረውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት የሚያስቀር ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ።
Next articleበወልቂጤ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።